ህዝብ ለውጥ ይፈልጋል። የሰው ልጅ በተፈጥሮው ለውጥ ፈላጊ ነው። ሰው የሚኖረው ለመለወጥ ነው። ለውጥ ለማምጣት የወደፊት የጉዞ መስመራችን መቀየስ ያስፈልጋል። የወደፊት የጉዞ መስመራችን ለመቀየስ ትክክለኛውን የፖለቲካ አቅጣጫ መምረጥ ይኖርብናል። ትክክለኛውን የፖለቲካ አቅጣጫ ለመምረጥ አማራጭ የሐሳብ መንገዶችን ማዘጋጀት ያስፈልጋል። አማራጭ የሐሳብ መንገዶችን ለማዘጋጀት የተለያዩ የየራሳቸው አማራጭ መንገድ ያላቸው ተቃዋሚ (አማራጭ መንገድ አቅራቢ) የፖለቲካ ፓርቲዎች መኖር አለባቸው። […]
