የሽመልስ ከማል ነገር… ከሙያ አጋሬ ሲሳይ አጌና ጋር አሪፍ እራት እየተመገበን ስለ አገራችን ፖለቲካ ስናወራና በጣልቃ ሽመልስ ከማልን አነሳን። ሲሳይ እንዲህ አለ፥ « እኔ ሁሌም የሚገርመኝ የሽመልስ ነገር ነው፤ ሌሎቹ ባለስልጣናት እንደ እንስሳ የሚነዱና በህሊናቸው የማይመሩ በመሆናቸው ተግባራቸው ብዙም አያስገርምም። ሽመልስ እኮ በአንድ ወቅት የኢትኦጵ ዋና አዘጋጅ ክስ ተመስርቶበት ሳለ «በነፃ ጥብቅና እቆማለሁ» ያለን ሰው […]
