ከውጭ የተመለሱ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ ቢፈልጉም፣ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉ የቢሮክራሲ ችግሮች ፈተና እንደሆኑባቸው ገለጹ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአገር ውስጥ በተለያዩ የኢንቨስትመንትና የሙያ ዘርፎች ከተሰማሩ ተመላሽ የዳያስፖራ አባላት ጋር ለመወያየት ባዘጋጀው መድረክ፣ ከ500 በላይ የዳያስፖራ አባላት ተገኝተው ችግሮቻቸውንና ምሬታቸውን ለመንግሥት አሰምተዋል፡፡ በሆቴልና ቱሪዝም፣ በንግድ፣ በማዕድን ፍለጋ ሥራና በትራንስፖርትና ማሽነሪዎች ኪራይ ላይ የተሰማሩ ከውጭ […]
