በዚህ ርእስ ላይ የምጽፈው ሃይማኖትን ለመስበክ ፈልጌ አይደለም፤ ከውስጥ የሚኮረኩረኝን ነገር ለማውጣት ነው፤ በኢትዮጵያ የተስፋ ሕልም አይታየኝም፤ የሚታየኝ የጥፋት ቅዠት ነው፤ ከሃያ ዓመት በላይ በመለስ ዜናዊና በጓደኞቹ በኩራትና በእብሪት የተዘራው ጥላቻ የኢትዮጵያ ሕዝብ ልቡ የደም መግል እንዲቋጥር አድርጎታል፤ ይህንን የማይገነዘብ ያለ አይመስለኝም፤ ነገር ግን ባህል ሆኖብን አደጋ ማስጠንቀቂያን አንወድም፤ በአንጻሩ ግን በባዶ ሜዳ ለሽለላና ለፉከራ […]
