ከግማሽ ሚሊዮን እስከ 2 ሚሊዮን ብር ካሣ የተከፈላቸው ገበሬዎች አሉ በተከፈላቸው ካሣ ንድግ ጀምረው የተሳካላቸው ጥቂቶች ናቸው “ቦታው ለሪል እስቴትና ለልማት ይፈለጋል ተብለን የእርሻ መሬታችንና የመኖሪያ ቦታችን በመንግስት ከተወሰደብን አራት አመታት ሞላን” ይላሉ – በሰበታ አዋስ ወረዳ እያረሱ ይኖሩ እንደነበር የገለፁ አርሶአደሮች፡፡ ለእርሻ መሬት እንደየስፋቱ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ የተከፈላቸው ገበሬዎች መኖራቸው አይካድም፡፡ […]
