ባለፈዉ ታሕሳስ አጋማሽ የተጀመረዉ ጦርነት አንዳድ ግምቶች እንደሚጠቁሙት በአስር ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ ገድሏል።ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ አፈናቅሏል።ወይም አሰድዷል።ከሰወስት ሚሊዮን የሚበልጥ ለረሐብ አጋልጧል።ጦርነቱ እስከ መጪዉ የዝናብ ወቅት ከቀጠለ ደግሞ—– ታሕሳስ ጦርነት ገጠሙ።ጥር የተኩስ አቁም ሥምምነት ተፈራረሙ።ተኩስ ግን አላቆሙም።ባለፈዉ አርብ እንዳዲስ ተኩስ አቁም ዉል ተፈራረሙ።ዛሬም ይቃዋጋሉ።እንዳዲስ ይወነጃጀላሉ። የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና የአማፂያኑ መሪ የቀድሞዉ ምክትል […]
