ለአለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት የሕዝብን መብት በመቀማትና አፍኖ በሥልጣን ላይ የሚገኘው የህወሃት/የኢህአዴግ መንግሥት ዜጐች በአገራቸው ውስጥ በመዘዋወር ሰርተው እንዳይኖሩ ያገደ ብቻ ሳይሆን በተወለዱበትና እየኖሩበት በአለው ቀያቸውም የገዠው ፓርቲ አባል ካልሆኑ ወይም ደግፈው ካልቆሙ ይሰደዳሉ፣ ይበታሰራሉ፣ ይደበደባሉ፤ በተለያዩ ምክንያቶችም ንብረታቸውን ይቀማሉ፡፡ የተቀዋሚ ፖለቲካ ድርጅት አባል ከሆነ ደግሞ ጫናው ምን ያህል እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ በዚሁ መመሪያቸው መሠረትም […]
