ኢሳት ዜና :-በጀርመን-ባየርን ክልል የሚገኙ ወደ 60 የሚጠጉ ኢትዮጰያውያን ስደተኞች የረሀብ አድማ ለማድረግ የተገደዱት የኢትዮጵያ ስደተኞች ጉዳይ በጀርመን ካሉ አካባቢዎች በተለየ መልኩ በባየርን ክልል እና ፍርድ ቤት ተቀባይነት ስለማያገኝ ነው። በከተማ መሀል ላይ በመሰባሰብ ባለፈው ረቡእ የተጀመረው የኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች የረሀብ አድማ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት የሶሪያ፣የሊቢያ እና የኢራቅ ስደተኞችም በአድማው ከኢትዮጵርያውያኑ ጋር እየተቀላቀሉ ነው። […]
