“‹‹የታሰራችሁ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያኖች የእኔ ጀግኖች ናችሁ። አከብራችኋላሁ።›› ብለህ ንገርልኝ አለኝ – ደጋግሞ።…” ከትናንት በስትያ ሰኔ 03 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ከቅርብ ጓደኛዬ እና የሙያ ባልደረባዬ ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ ጋር ወደቃሊቲ ማረሚያ ቤት [እስር ቤትም ነው] አምርተን ነበር- ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና የአንድነት ፓርቲ ጸሐፊ የሆኑትን አቶ አንዷለም አራጌን ለመጠየቅ። የተለመደውን የፖሊስ ፍተሻ አልፈን […]
