Quantcast
Channel: Freedom4Ethiopian
Viewing all articles
Browse latest Browse all 4543

ኢትዮጵያ በፍርሀት የሞት እና ሽረት ትግል መካከል የምትንጠራወዝ ምስኪን አገር፣

$
0
0
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ (የጸሐፊው ማስታወሻ)፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ገዥ አካል  በቅርቡ ገንቢ ያልሆነእና በእራስ አሸናፊነት ጎልቶ ለመውጣት በሚል ዕኩይ ምግባር በተቃዋሚዎቹ እናትችት በሚያቀርቡበት ወገኖች ላይ እየወሰደ ያለውን የቅጣት እርምጃ አሳፋሪ ነው::ገዥው አካል በተደጋጋሚ በሚሰራቸው አስቂኝ የስህተት ቀልዶች (በሚከተላቸውብልሽቶች እና ድሁር አቅመቢስነት) እና በሚፈጽማቸው የመድረክ ትወናዎች(ለአጭር ጊዜ እኩይ ፍላጎቱ እርካታ ሲል በሚያራምዳቸው ውዥንብሮቹ) በሁለቱምድርጊቶቹ የሚያስደንቅ እና ግራ የሚያጋባ ሆኗል ፡፡ ገዥው አካል ለምንድን ነው 20እና ከዚያ በላይ የሚሆኑ ጦማሪያንን እና በጣት የሚቆጠሩ ሃያሲ ጋዜጠኞችን ሸፍጥበተመላበት ሁኔታ በሀሰት በተፈበረከ እራሱ “አሸባሪነት” እያለ በሚጠራው ክስ ከሶበእስር ቤት አጉሮ ንጹሀን ዜጎችን እያማቀቀ ያለው? ለምንስ ነው ክቡር የሆነውንየጋዜጠኝነትን ሙያ እየወነጀሉት ያለው? ለምንድን ነው ገዥው አካል የአገሪቱንኢኮኖሚ በመዳፉ ስር ጨምድዶ ይዞ  በተጠንቀቅ በአንድ ቦታ ቆሞ የሚጠባበቅወታደራዊ ኃይል እያለው እና ብዛት ያላቸው ጠብመንጃዎች፣ ታንኮች እና የጦርአውሮፕላኖች በእራሱ ቁጥጥር ስር እያሉት በጥቂት ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ልቡበፍርኃት እየራደ በጭንቀት ማዕበል ውስጥ እየዋኘ የሚገኘው? ጉልበትን እንጅ ህግንእና ስርዓትን የሚጠየፈው ገዥ አካል በነጋ በጠባ ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ በመፎከር የራሱ ጥላ አያስበረገገው ተሸበሮ የሚሸበረው?  በገዥው አካል በኢትዮጵያ የፕሬስ እና ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት እየተሸረሸረበማለቁ እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞችን ወደ እስር ቤት እያጎረያለበት ሁኔታ በመፈጠሩ ምክንያት ኢትዮጵያ “13 የብርሀን ወራት ያላት አገር “መባሏ ቀርቶ ይልቁንም  በጨለማው አህጉር “13 ወራት የጨለማ አገር” ተብላለች ፡፡ በጣም ያስገርመኛል! ያ ገዥ አካል በእራሱ የፖለቲካ ምህዋር የሚዞር እና እንደገደል ማሚቶ እያስተጋባ የሚኖር የእራሱ ነጻነት የሌለው ግኡዝ አካል ነውን? ከዚህአንጻር በኢትዮጵያ ስርዓቱን የሚያሽከረክረው ገዥው አካል በፍርሀት ቆፈን ውስጥተወሽቆ የሞት ሽረት ትግል እያደረገ ያለ ሆኖም ግን በዞን 9 ጦማርያን እና ሰላማዊህዝብ እንቅስቃሴ  እያወደመ  የሚኖር የሽብር መንግስት ሆኗል፡፡ ) በሞት  ሽረት  ትግል  ውስጥ  የሚገኙት  የዞን 9  ትንታግ  ወጣት  ጦማርያን የኔ ጥያቄ እውን በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው ስርዓት “የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሬፐብሊክ መንግስት” ነው ወይስ በሽብር ተግባር ላይ ተዘፍቆ የሚገኝ “የፖሊስ መንግስት”? ኢትዮጵያ በሌላ ጠፈር (ህዋ) የምትገኝ አገር ናትን? እነዚህን ጥያቄዎች በጥሞና የማነሳቸው ጥያቄዎች ናቸው፡፡ […]

Viewing all articles
Browse latest Browse all 4543