ነፍሱ ጣር ላይ እያለች በብልቱ ሲጫወቱበት ነበር ያለሁበት የመን ውስጥ የማይሰማ አይነት ስደተኞች ላይ የሚደርስ ስቃይ የለም፡፡ የስቃይ አይነቱ ተቆጥሮ የማያልቅ ነው፡፡ኢትዮጵያዊን ስደተኞች ከጅቡቲ ቀይ ባህር እና ከሶማሊያ ህንድ ውቅያኖስን ተሻግረው ወደ የመን ይገባሉ፡፡ ግባቸው ግን የመን በመድረስ የሚገታ አይደለም፡፡ ይቀጥላሉ፡፡ አላማቸው የተስፋይቱ ምድር ናት የተባለ ይመስል ሳዑዲ አረቢያን ያነጣጠረ ነው፡፡ ሳዑዲ እጇን ዘርግታ በሳቅ […]
