ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ በአንድ ሀገር የተረጋጋ የፖለቲካ ስርዓት ዘላቂ ሰላም መልካም አስተዳደርና የልማት ተነሳሽነት ሊኖር የሚችለው የህዝብ የስልጣን ባለቤትነት በተግባር ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ የህዝቡ የስልጣን ባቤትነት የሚረጋገጠውም ወቅቱን ጠብቆ በሚካሄድ ሁሉን አቀፍ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ነው፡፡ ይሁን እንጅ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅሜን ያሰጠብቁኛል፣በትክክል ያገለግሉኛል ይበጁኛል ብሎ ያመነባቸውን ተወካዮቹን በነጻነት በመምረጥ ዕውነተኛ […]
