• ለስልጠናው 2,345,000 ብር ይወጣል ለተማሪዎች፣ ለነዋሪዎች፣ ለመምህራንና ለሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ሲሰጥ የቆየውን የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን በነገው ዕለት እንዲጀምሩ የተነገሩት የከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች ስልጠናውን መቃወማቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ ነገ መስከረም 19/2007 ዓ.ም በሚጀምረው ስልጠና 4100 የከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች እንዲሳተፉ ትዕዛዝ የተላለፈ ሲሆነ ሰራተኞቹ ግማሹን ቀን ሰልጥነው ግማሹን ቀን እንዲሰሩ ይደረጋል ተብሏል፡፡ ይህንም […]
