የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ቀደም ሲል ግንቦት 22/2005 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ የመከላከያ ምሥክሮቹን ዛሬ – ማክሰኞ ሐምሌ 2/2005 ዓ.ም ማሰማት ጀምሯል፡፡ ዶ/ር ያሬድ ለገሠ እና ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ለምሥክርነት ቀርበዋል፡፡ “የመንግሥትን ስም ማጥፋት” የሚለው ድንጋጌ ሃሣብን ከመግለፅ መብትና ከሃገሪቱ ሕገመንግሥትም ጋር የሚቃረን መሆኑን የሕግ ምሁሩ ዶ/ር […]
