በበትረ ያዕቆብ ————————- ትናንት በማለዳ ነበር ተነስቼ ከሰሚት ወደ ሳሪስ ያቀናሁት፡፡ የሐምሌን ቀዝቃዛ የጠዋት አየር እየተመገብኩ ከጓደኞቼ ጋር ከተቀጣጠርኩበት ሐበሻ ካፌ ስደርስ ሰዓቴ ከጥዋቱ 1፡30 ይል ነበር፡፡ ሁላችንም ከየአቅጣጫዉ በዚያች አነስተኛ ካፌ ከተሰባሰብን በኋላ ቁርስ ቢጤ እንደ ነገሩ ቀማምሰን የዕለቱን ዕቅዳችንን ለመፈፀም ተነሳን—በልባችን ስኬትን እየተመኘን፡፡ እናም ፍራፍሬ በየአይነቱ ሸማመትን ፤ ያስፈልጋሉ ያልናቸዉን ነገሮች ሁሉ አሟልተን […]
