ታሪኩ ዝዋይ እሥር ቤት ወንድሙን ለማየት ይገባል። እዚያም፣ “ተመስገንን ጥሩልኝ ” ሲል ፖሊሶችን ይጠይቃል። በዚህ ግዜ የመቶ ዓለቃ ማዕረግ ያለው ወታደር (ፖሊስ) ተመስገንን መጠየቅ እንደማይችል ይነግረዋል። ታሪኩም “ምን ተፈጠረ ወንድሜን እንዳልጠይቀው የተከለከልኩት ?” በማለት ለፖሊሱ ጥያቄ ያቀርባል። ፖሊሱም በማመናጨቅ “ውጣ” ይለዋል። ነገሩ ያላማረው ታሪኩ ለወንድሙ ያመጣውን ስንቅ እንደያዘ ወደ በሩ ያመራል። ነገር ግን” ውጣ” ያለው […]
