በአንድ ወቅት ኢህአዴግ «የሚወዳደረኝ ተቃዋሚ ጠፋ» ብሎ ቀልዶ ነበር። በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ተበታትነው የነበሩት ተቃዋሚዎች ቅንጅትን ፈጥረው 1997 ምርጫ ላይ ሲያሸንፉት ደግሞ ቀልዱን ረስቶት ወደ ምርጫ የሚያመራውን መንገድ ሁሉ ለመዝጋት መታተር ያዘ። የፀረ ሽብር፣ የፕሬስ፣ የሲቪክ ማህበራት….አዋጆች «ከእኔ ጋር ለመወዳደር አቅም የላቸውም።» ይላቸው የነበሩትን ተቃዋሚዎች ወደ ምርጫ የሚያመሩበትን መንገድ የሚዘጉ መሰናክሎች ሆኑ። ያም ሆኖ ግን […]
