ኢሳት ዜና :- ባለፈው ወር ሄሊኮፕተር ይዘው የጠፉት ሻምበል ሳሙኤል ግደይ፣ መቶ አለቃ ቢልልኝ ደሳለኝ እና ቴክኒሻን ጸጋ ብርሃን ግደይ በተረጋጋ እና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለኢሳት ገልጸዋል። ፓይለቶቹ በሚገኙበት ሶስተኛ አገር ውስጥ ሆነው ከኢሳት ጋር ግንኙነት የመሰረቱ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚደረገው የነጻነት ትግል አስተዋጽኦ ለማድረግ መዘጋጃታቸውን ተናግረዋል። ሶስታችንም በአንድ ላይ የምንመደብበትን ጊዜ ስንጠብቅ ቆይተን […]
