የፕራይቬታይዜሽንና የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የመንግስት ልማት ድርጅቶችን መሸጥ ከጀመረበት ከ1997 ዓ.ም እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ ባሉት ጊዜያት ከሸጣቸው 370 ድርጅቶች መካከል ሼህ አልአሙዲ ወደ 30 የሚጠጉትንና እጅግ አትራፊ የሆኑ ድርጅቶችን በርካሽ ዋጋ መሰብሰብ መቻላቸው ስርአቱ ለተዘፈቀበት ሙስና ማሳያ መሆኑን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ገልጸዋል። ሼሁ የለገደንቢን ወርቅ ማዕድን በአሁኑ ወቅት ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኩባንያ እየተባለ የሚታወቀውን በ1989 ዓ.ም በብር 1 […]
