በማዕከላዊ እስር ቤት ታስረው የሚገኙት ብርሃኑ ተክለያሬድና ፍቅረ ማሪያም አስማማው አብራቸው በታሰረችው እየሩስ ተስፋው ላይ እየተፈፀመ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በመቃወም የርሃብ አድማ መቱ፡፡ ብርሃኑና ፍቅረማሪያም ከትናንት የትንሳኤ በዓል ጀምረው የእርሃብ አድማ ያደረጉ ሲሆን በትናንትናው ዕለት የገባላቸውን ምግብ እንዳልበሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡ እየሩሳለም ተስፋው ከሳምንት በላይ ብቻውን እንድትታሰር ተደርጋ ከፍተኛ ምርመራ እየተደረገባት ሲሆን ከቤተሰቦቿ ጋር እንዳትገናኝ […]
