በተላያዩ ብዙ ፈተናዎች መሀከል አልፈው መምህሩ ዛሬ ያሉበት ደረጃ ደረሱ፡፡ ዛሬ እንደድሮው የሚታለል ሕዝብ እያነሰ በእሳቸው ትምህርሕርት ራሱን እያወቀ ለእግዚአብሔር የሚንበረከክ ሕዝብ እየበዛ መጣ፡፡ ፈታኞቹ ግን ዛሬም ተስፋ አልቆረጡም፡፡ ፈተናው ግን የአንዱ የመምህር ግርማ ሳይሆን የሕዝብ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላም ፈተናውን መወጣት የሕዝብ ድርሻ ነው፡፡ እስከዛሬ ሕዝብ እስከሚገባው በሚል መምህሩ ብቻቸውን ፈተናዎችን ሁሉ በመጋፈጥ መስዋዕት ሆነው […]
