የ1997 ምርጫ በኢህአዴግ ኮሮጆ ገልባጭነት ወደ ሁከት ከተቀየረ በኋላ አገሪቱ ወደ ወህኒ ማዕከልነት ተለወጠች፡፡እፍርታሙ ኢህአዴግ ከቅንጅት አመራሮች አንስቶ ጋዜጠኞችን፣የሲቪክ ተቋማት አመራሮችንና ተራውን የህብረተሰብ ክፍል ጭምር በጊዜያዊነት ወዳዘጋጃቸው ማጎሪያቸው ወሰደ፡፡ መች በዚህ ብቻ በቃቸው፡፡አልያዝናቸውም ያሏቸውን ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ፎቶግራፍ በሚቆጣጠሩት ቴሌቭዥን አማካኝነት በመለጠፍ ‹‹እጅ ስጡ››ማለቱን ተያያዙት፡፡እንፈልጋቸዋለን ካሏቸው ጋዜጠኞች አንዱ እስክንድር ነጋ ነበር፡፡ በዚያው ሰሞን አንድ የኢትዮጵያ አየር […]
