”…ፍትሕ ሚኒስቴር በቅርቡ ‹‹በሥነምግባር ችግር›› በሚል የተማምን የጥብቅና ፍቃድ በመሰረዝ ለአንድ ዓመት ከሰባት ወራት እንዳገደው የሚታወቅ ነው፡፡….ተማም ብዙ ጊዜውን በቤቱ በማንበብ ነበር ጊዜውን የሚያሳልፈው፡፡ በጨዋታ መካከል ስለባልደረባችን ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ መታሰር ነገርኩት፡፡ ደነገጠ፡፡ ‹‹አጃኢብ›› አለና ‹‹በምን?›› አለኝ በጣም አዝኖ፡፡ ‹‹የአልሸባብ ህዋስ ነህ፤ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በሚገኙበት ስብሰባ ላይ የሽብር ድርጊት ለመፈጸም አሲረሃል›› ተብሎ ተጠርጥሮ መያዙን […]
