ባለፈው ቅዳሜ በተነሳው ግጭት ከፖሊስና ከመከላከያ አንዳንድ ወታደሮች ቆስለዋል። የግጭቱ መንስኤ ሁለት የመከላከያ ፖሊስ አባላት በፖሊሶች መደብደባቸው ነው። ከዚህ ቀደም አንድ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ፍቼ አካባቢ ሰፍሮ የሚገኘውን የመከላከያ ሰራዊት አባል ከገደለው በሁዋላ፣ በመከላከያና በፖሊስ መካከል ለወራት የዘለቀ ቁርሾ እንዲፈጠር አድርጓል። ባለፈው ቅዳሜ ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት በከተማው እየተዝናኑ በነበረበት ወቅት፣ ፖሊሶቹ የደበደቡዋቸው ሲሆን፣ የመከላከያ […]
