በአቶ ማሙሸት አማረ ካቢኔ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የነበረው አቶ አብርሃም ጌጡ ዛሬ ጥቅምት 6/2008 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት ቀርቦ ለህዳር 4/2008 ዓ.ም ተቀጥሮበታል፡፡ በዛሬው ችሎት ፖሊስ ‹‹እስካሁን ካልተያዙ ግብረ አበሮቹ ጋር ለሽብር ተግባር ከውጭ ሀገር የተላላከውን ገንዘብ ባንኮች ሪፖርት ስላላኩልኝ፣ ከግብረ አብሮቹ ጋር የተለዋወጠውን መረጃ አስተርጉሜ ስላልጨረስኩና የሰው ማስረጃዎች ስላለኝ›› […]
