ህወሓት በ1983 ዓ.ም መላ አገሪቱን በነፍጥ እንደተቆጣጠረ በሁለት ያለፉ የኢትዮጵያ መንግስታት ከፍተኛ የህዝብ ሀብት፣ ዕውቀትና ጉልበት ፈሶበት ለዘመናት በስንት ልፋትና ጥረት የተገነባውን የአገር መከላከያ ሰራዊት ባደረበት ጭፍን ጥላቻና ቂም ብቻ ተመስርቶ “የደርግ ነው” በሚል ሰበብ ባንድ ጀምበር ንዶ ማፈራረሱን አገር ያወቀው ፀሃይ የሞቀው ሀቅ ነው፡፡ ከበረሃ የመጡ ድኩማን ታጋዮቹን ለሙያው የሚመጥን ምንም አይነት ዘመናዊ ዕውቀት […]
