በከፍተኛ ድርቅ ተመትተው ነዋሪዎቻቸው ክፉኛ ለጠኔ ተጋልጠው የሚልሱት የሚቀምሱት በማጣታቸው ከሞት አፋፍ ላይ ሆነው የሚገኙባቸው አምስቱ ቀበሌዎች ጨጨሆ፣ ፈንጠርያ፣ ቀንጠብጣ፣ አይጠላ እና እንድ ሌላ ለጊዜው ስሙን ያላወቅነው ቀበሌ ናቸው፡፡ በሰሜን ጎንደር የወገራ ወረዳዎቹን ሶሚያ፣ ጓሪ፣ ግጭሆ እና ቧግሽ የተባሉትን አራት ቀበሌዎች ጨምሮ እስካሁን ዘጠኝ ቀበሌዎች ክፉኛ በድርቅ ተመትተው ከ50ሺህ እስከ 60 ሺህ ህዝብ ተርቦ የስደትና […]
