ከድርቁ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያና የኬንያ አዋሳኝ ከተማ በሆነችው ሞያሌ ከተማ፣ የአተት ወረርሽኝ ተከስቶ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ወደ 90 ገደማ የሚሆኑ በበሽታው ተይዘው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለአዲስ አድማስ አስታውቋል፡፡ በከተማው በአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አተት) ተይዘው በጤና ተቋማት የታከሙት 91 ያህል ሲሆኑ 71 ህክምናቸውን ተከታትለው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ፣ 18 ደግሞ እስከ ትናንት በስቲያ […]
