ሪፖርተር፡- እርስዎ 10 ሺሕ ሔክታር ጠየቅሁ ቢሉም እኛ የምናውቀው ግን 300 ሺሕ ሔክታር መሬት እንደተቀበሉ ነው፡፡ ይህ እውነት አይደለም እንዴ? ራም ካሪቱሪ፡- የተመዘገበና በየትኛውም ፍርድ ቤት ላረጋግጠው የምችለው ሀቅ አለኝ፡፡ የጋምቤላ ክልል መንግሥት ካቢኔ በሙሉ ስብሰባ ከተቀመጠ በኋላ 10 ሺሕ ብቻማ አንሰጥህም አሉኝ፡፡ እኔ ግን አቅሜ ይኸው ብቻ እንደሆነ ገልጬላቸዋለሁ፡፡ ከስብሰባቸው በኋላ 300 ሺሕ ሔክታር […]
