የሶማልያ የወደብ ከተማ የሆንችዉን ኪስማዩ ከሶማሊያዉ ታጣቂ ሀይል አል-ሸባብ ለማስለቀቅ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ወታደሮችንና ታንኮችን ወደ ስፍራዉ ማሰማራቷ ተገለጠ። የታጣቂ ሀይሉ ጠንካራ ይዞታ እንደሆነች የሚነገርላትን ኪስማዩ ለማስለቀቅም በአካባቢዉ በማንኛዉም ሰአት ከባድ ዉጊያ ይቀሰቀሳል የሚል ስጋት መኖሩን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታዉቀዋል። እሑድ ወደ ወደባማ ከተማዋ የገቡት በመቶዎች የሚቆጠሩት የኢትዮጵያ ወታደሮች በታጣቂ ሀይሉ ቁጥጥር ስር የምትገኘዉን ከተማ ነጻ ለማዉጣት […]
