የኢህኣዴግ መንግስት ዓይኑን ጨፍኖ የሚያወጣቸው ኣዋጆች፣ እቅድና ኣሰራሮች ህዝቡን ኣማርሮ ለዓመፅ እየገፋፋው ነው። ሰሞኑ የመቐለ መስተዳድር በከተማዋ የሚገኙ ከ2500 በላይ ባለ ባጃጆች የሚመለከት ያወጣውና “ባጃጆች በታፔላና በሚወጣላቸው መስመር ብቻ እንዲሰሩ” የሚያስገድድ ኣሰራር ከፍተኛ ተቃውሞ ኣጋጥሞታል። መስተዳድሩ “ባጃጆች እንደ ታክሲ ታፔላ ተለጥፎባቹ፣ በተመደባቹ መስመር ብቻ መሰራት ኣለባቹ፣ ማንኛውም ኮንትራት መስራት ኣይፈቀድም፤ ይሄ ኣሰራር ፀጥታችን ኣስተማማኝ […]
