የኢትዮጵያ ዋነኛ የልማት አጋር የሆነው የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በህብረቱ ዋና መቀመጫ ብራሰልስ ከተማ ተገኘተው በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ስላለው ተቃውሞ ማብራሪያን እንዲሰጡ ጠየቀ። ሆኖም የተዘጋጀላቸውም ጋዜጣዊ መግለጫ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ተሰርዟል። የቀረበላቸውን ጥያቄ ተከትሎ በብራሰልስ የሚገኙት ዶ/ር ቴዎድሮስ በጉዳዩ ዙሪያ ከህብረቱ አባል ሃገራት በርካታ ጥያቄዎች ይቀርብላቸዋል ተብሎ በመጠበቅ ላይ መሆኑን […]
