ሐዋሳ ከተማ ለስድስተኛ ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ማስተናገዷን ተከትሎ በቀጣይ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አለመታወቁ ስጋት በነዋሪዎቿ ላይ ተፈጥሯል ። ተደጋጋሚው የመሬት መንቀጥቀጥ በፈጠረው ስጋት የተነሳም ህዝቡ ወደ መኖሪያ ቤቱ ለመግባት ተጨንቋል። በከተማው የሚገኘው ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችም ከትናንቱ የመጀመሪያ አደጋ ጀምሮ ማደሪያቸውን በመልቀቅ ግቢው ውስጥ መሬት ላይ ለሊቱን ለማሳለፍ ተገደዋል ።ዛሬም ሁኔታው ለውጥ ባለማሳየቱ ተማሪዎቹ ዶርማቸውን ለመጠቀም አልሞከሩም […]
