መንግስት ያወጣዉን የመሬት ይዞታ አዋጅ በመቃወም ዛሬ በድንገት የተደረገዉ ሰልፍ ፖሊሶች ህዝቡን መቆጣጠር ተስኖአቸዉ በህዝብ ቁጥጥር ስር የዋሉበት አጋጣሚ እንደነበር የሰልፉ ታዳሚዎች ያስረዳሉ። መንግስት ከአያት ቅድመ አያቶቻችን የወረስነዉን መሬት እየቀማ ለኢንቨስተሮች ይሰጥብናል የሚሉት የቡታጅራና የአካባቢዉ ነዋሪዎች ተወልደን ባደግነበት ቀዬ እንድንፈናቀል ተደርገናል ሲሉ ቅሬታን ያሰማሉ። የአካባቢዉ ነዋሪዎች ለቢቢኤን እንደገለጹት ልክ የአዲስ አበባዉን የሚመስል ማስተር ፕላን በድብቅ […]
