በተጠረጠሩበት የሽብር ድርጊት ወንጀል የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ‹‹መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ ተሰናብተዋል›› ቢላቸውም፣ ይግባኝ ተጠይቆባቸው በእስር ላይ ሆነው እየተከራከሩ የሚገኙት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ (አንድነት) ፓርቲ፣ የአረና ፓርቲና የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የነበሩት ሕይወታቸው አደጋ ውስጥ መሆኑን፣ ለይግባኝ ሰሚው ችሎት የካቲት 1 ቀን 2008 ዓ.ም. አሳወቁ፡፡ አቤቱታቸውን ያቀረቡትና አመራሮች የነበሩት አቶ ዳንኤል ሺበሺ (አንድነት)፣ አቶ አብርሃ ደስታ […]
