አቡነ ማትያስ የጠሩት ስብሰባ ፓትርያርኩ በክርስቶስ ወኪልነት መከበር አለባቸው በሚል አምባገነናዊነትና ካቶሊካዊ አስተምህሮ ተደመደመ፡፡ ጤነኛ ተሰብሳቢዎችን ሳይቀር ባስገረመ ሁኔታ ከብፁዓን አባቶች ጋር መወያየቱን ትተው በሌላቸው ሥልጣን የመምሪያ ሓላፊዎችንና የኮሌጅ ተወካዮችን የሰበሰቡት ፓትርያርኩ ማኅበረ ቅዱሳንን በተለመደው ሁኔታ በመክሰስ መድረኩን ለተሰብሳቢዎች ከፈቱት፡፡ ፓትርያርኩ ማኅበረ ቅዱሳንን ለመክሰስ ይጠቅመኛል ብለው ያሰቡትን ምክንያትም ሰበብም (እውነቱንም ውሸቱንም) ደርድረው አንድ ነገር መባል […]
