በወልቃይት ሕዝብ የማንነት ጥያቄ ላይ ውሣኔ እንዲሰጠን ለፌደራል መንግሥት ባስገባነው ጥያቄ ምክንያት ዛቻና ወከባ እየደረሰብን ነው ያሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ስሞታ እያሰሙ ነው። በምዕራባዊ ትግራይ ዞባ በቃስታ ሁመራ ወረዳ ውስጥ በምትገኘውና ከሱዳን ጋር በምትዋሰነው ማይ ካድራ ቀበሌ ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች ፖሊስ ሰዉን እየጠራ እያስፈራራ ወረቀት ያስፈርማል ብለዋል። ቀበሌአችንን መገናኛ ብዙኃን አያውቁትም፤ ሃሣባችንን ተናግረን የፈለጉትን […]
