በኡጋንዳ በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዩዌሪ ሙሴቪኒን ይቀናቀናሉ ተብለው ግምት የተሰጣቸው ፖለቲከኛ ከሰዓታት በፊት በካምፓላ ፖሊስ ታስረዋል ።ምርጫው የሚከናወነው የፊታችን ሐሙስ ነው ። ዶክተር ኪዛ ቢሲጌ ከዚህ ቀደም ብዛት ባላቸው አጋጣሚዎች እየታሰሩ ቢፈቱም የአሁኑ ምርጫው ወደ ድምፅ መስጠት ሊሸጋገር ቀናቶች ሲቀሩት መሆኑ አነጋጋሪ ይሆናል ። ቢሲጌ በሶስት ፕሬዘዳንታዊ ምርጫዎች ተካፍለው ሶስቴም በሙሴቪኒ መረታታቸው ተነግሯል ።በአራተኛው አሸናፊ […]
