*‹‹ትዕዛዙ ግልጽ አልሆነልንም›› ማ/ቤት *‹‹ይሄ የፍ/ቤቱን ትዕዛዝና ህገ-መንግስቱን አለማክበር ነው›› ዳኛ ዳኜ መላኩ በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከተከሰሱበት የሽብር ወንጀል ነጻ እንደሆኑ ተበይኖ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ከተሰጠላቸው ሰባት ወራት ያስቆጠሩትና አሁንም በእስር ላይ የሚገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች እነ ሀብታሙ አያሌው ዛሬም ጠ/ፍ/ቤት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ከእስር ሊፈቱ አለመቻላቸው ታውቋል፡፡ ዛሬ የካቲት 7/2008 […]
