ሶማሊያ ዉስጥ የሚንቀሳቀሰዉ ታጣቂ ቡድን የአልሸባብ ተዋጊዎች በከፊል ራስ ገዝዋ ፑንትላንድ የሚገኝ ትንሽ ወደብ መያዛቸዉን ሮይተርስ ዘገበ። ባሳለፍነው የፈረንጆች አመት የአፍሪቃ ኅብረት የሶማሊያ ሰላም አስከባሪ « AMISOM» እና የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር አል ሸባብን በስፋት ከተቆጣጠረዉ ደቡባዊ የሶማሊያ ግዛት ማስለቀቃቸዉ ይታወሳል። እንደ ባለስልጣናት ገለፃ በዚያን ጊዜ የአሸባብ ተዋጊዎች የአፍሪቃ ኅብረት የሰላም አስከባሪዉ የጦር ኃይል «AMISOM» ከሚቆጣጠረዉ […]
