ፕሮፌሰር ባህሩ ይህን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ከምሁራን ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ይለማርያም ውይይቱን ሲከፍቱ ባሰሙት ንግግር፦”መንግሥት ኅብረተሰቡን ለማንቀሳቀስ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን፣ እንዲሁም ሌሎች ፕሮጀክቶችን አገራዊ መግባባት ለመፍጠር በሚያስችል አኳኋን ቀርፆ ተግባራዊ ለማድረግ እየጣረ ቢሆንም፣ ፖለቲከኛው ጥግ ጥጉን ይዞ ከመታኮስ ባለፈ የመቻቻልና የመወያያት ዴሞክራሲያዊ ባህልን ማዳበር አቅቶታል” ብለዋል። አቶ ሀይለማርያም […]
