ዛሬ ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው የኖርዌይ ዜግነት እንዳላቸው የሚነገረው የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ በተከሰሱበት የሽብር ወንጀል ጥፋተኛ ተብለዋል:: በአኙዋክና ኑዌር ጎሳዎች መካከል ከተፈጠረው ግጭት ጋር ተያይዞ ከሀገር የተሰደዱት አቶ ኦኬሎ፣ የብዙዎችን ህይወት የቀጠፈው ግጭት የተቀናበረውና በግድያውም የተሳተፉት የመንግስት ወታደሮች እንደነበሩ ለተለያዩ የዜና አውታሮች መግለፃቸው ይታወሳል። ከአቶ ኦኬሎ ጋር በአባሪነት የከሰሱ ሌሎች […]
