መንግስት እንደፈለገ የግል የኮምፒውተር መረጃዎችን መጥለፍ፣ መበርበር፣ መሰለል፣ ኦን ላይን መፈለግ የሚያስችለውን ህግ አርቅቆ ለፓርላማ አቅርቦአል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ኮምፒውተር ወይንም የኮምፒወተር ስርዓት ምንነት ሲያብራራ በሶፍትዌር እና ማይክሮቺን ቴክኖሎጂ ላይ የተመሠረተ የዳታ ፕሮሰሲንግ፣ ክምችት፣ ትንተና፣ ስርጭት፣ ግንኙነት ወይንም ሌሎች ሂሳባዊ ወይንም አመክኖአዊ ተግባራትን የሚያከናውን ማንኛውም መሳሪያ ነው ይለዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ የኮምፒውተር ወንጀል በፈቃድ እና ለፈቃድ እንደሚከናወን […]
