ከጋምቤላ ከተማ በስተምስራቅ 17 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው ጃዊ የስደተኞች ካምፕ አቅራቢያ ኢትዮጵያዊው ሹፌር በደቡብ ሱዳናዊው ስደተኛ ላይ ላደረሰው የመኪና አደጋ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በሰጡት ምላሽ 14 ኢትዮጵያዊያን የጭካኔ ድርጊት ተፈጽሞባቸው ለሞት መብቃታቸውን ከአካባቢው የተገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ በስደተኞቹ ካምፑ ለሚገኙ ደቡብ ሱዳናዊያን አገልግሎት የሚሰጡ የእርዳታ ሰራተኞች ለማመላለስ በሹፍርና ስራ የተቀጠረው ኢትዮጵያዊ አንድን ደቡብ ሱዳናዊ በሚያሽከረክራት […]
