አልኑር በሽር ሲባል በቆየ በቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል በጉባ ወረዳ በኦሜድላ ቀበሌ ባለ እርሻ ልማት ላይ የሚሠሩ 22 ሠራተኞች በሱዳን ወታደሮች ተጠልፈው መወሰዳቸውን የእርሻ ልማቱ ባለቤት ነኝ ያሉት አቶ ይርሳው የሺወንድም ተናግረዋል። አቶ ይርሳው ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል ባለፈው ቅዳሜ፤ ሚያዝያ 22 / 2005 ዓ.ም በሁለት ተሽከርካሪዎች የደረሱ የሱዳን ወታደሮች የያዟቸውን ሠራተኞቻቸውን ዲቫዚን የምትባል የሱዳን ከተማ ወይም […]
