ሁለቱ ሱዳኖች የይገባኛል ጥያቄን አንስተው በሚገኙባት የአብዬ ግዛት በሰላም ማስከበር ስራ ላይ ተሰማርተው ከሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች መካከል በተለያዩ ጊዜያት የሞቱ ወታደሮች ቁጥር 16 መድረሱን የተባበሩት መንግስታት የልዑካን ቡድን ገለጠ። የሰላም አስከባሪ ቡድኑ ሰላም ማስከበር ስራ ላይ ተሰማርተው ህይወታቸው ላጡ ወታደሮች ቤተሰቦች የክብር የሜዳሊያ ስጦታን ሰሞኑን በአብዬ ግዛት ማበርከቱን የሱዳን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ሁለቱ ሱዳኖች በነዳጅ […]
