ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ቁልፍ: ወሳኝ ተጽእኖ ፈጣሪ በሆኑ በኢኮኖሚው: ፖለቲካውና ጸጥታው ላይ በአንድም ይሁን በሌላ ተለይተው በሚታዩ ሀገራት ህወሀት አምባሳደሮችን በትግራይ ተወላጆች በሆኑ አባላቱ እየተካቸው ነው። በአውስትራሊያና ኒውዚላንድ ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማርያም ተሹመዋል። በእንግሊዝ በአቶ ብርሃኑ ከበደ ምትክ ዶ/ር ሃይለሚካዔል ቦታውን ይዘዋል። አሜሪካ ያሉት አቶ ግርማ ብሩ በህወሀቱ አቶ ብርሃን ኪዳነማርያም እንደሚተኩ ከውስጥ የወጣ መረጃ ያመለክታል። […]
