በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ሰኞ ዕለት የቀረቡት እነ አቶ በቀለ ገርባ አሁንም በጨለማ ቤት እንደሚገኙና ተፅዕኖች እንደቀጠሉባቸው ተገለጸ። ፍርድ ቤቱም ክሱ በሽብር ያስከስሳል አያስከስስም በሚል ውሳኔ ለመስጠት ከሃምሌ 25 ቀጠሮ በመስጠት መነሳቱም ታውቋል። በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰን ከመንፈቅ በላይ የቀጠለውን ተቃውሞ ተከትሎ በቁጥጥር ስር የዋሉት የኦፌኮ ምክትል ፕሬዚደንት አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች አመራሮች ከግንቦት […]
