በእንግሊዝ ፖርትስማውዝ ፖሊስ 28 ስደተኞችን መያዙን አስታውቋል፡፡ከስደተኞቹ መካከል ሁለት ሴቶችና አንድ ህጻን እንደሚገኝ የዘገበው የእንግሊዙ ዴይሊ ሜይል የስደተኞቹ ዜግነት 11 ኤርትራዊያን፣10 ሱዳናዊያንና ሰባት ኢትዮጵያዊያን ነው ብሏል፡፡ ስደተኞቹ በዕቃ መጫኛ መኪና ተጭነው ሲጓዙ ከቆዩ በኋላ ለመጸዳዳት በመውረዳቸው ለእይታ በመጋለጣቸው በቁጥጥር ስር ለመዋል በቅተዋል ተብሏል፡፡በሞባይል እንደተቀረጸ የተነገረለት የቪዲዩ ምስልም ስደተኞቹ ከፖሊስ ለማምለጥ ሲሯሯጡ ያሳያል፡፡የእሳት አደጋ መኪኖችና አምቡላንሶችም […]
