የኢትዮጵያ መንግስት አክቲቪስቱን አንዳርጋቸው ጽጌን በማፈን በህገ ወጥ መንገድ በማሰሩና በአገሩ ውስጥ በሚፈጽማቸው ጥሰቶች የተነሳ የአሜሪካ ሴናተሮች ኮሚቴ አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን እርዳታ እንድትመረምር ለማድረግ ጥሪ ለማቅረብ የሚያስችለውን ረቂቅ ለማጽደቅ የመነሻ ይሁንታን ከሰኔቱ ማግኘቱ ተሰምቷል፡፡ ረቂቁ ‹‹ድጋፍ ለሰብዓዊ መብት መከበርና መልካም አስተዳደርን በኢትዮጵያ ማበረታታት››የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን በሰኔቱ የህግ አውጪዎች ስብሰባ ወቅት የመጀመሪያውን ደረጃ ለማለፍ የሚያስችለውን […]
